Tender Detail

Tender Details


የሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተጠቀሱ ለተለያዩ ሰራዎች እና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1: የፅህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ልቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፤ የስፖርት አልባሳትና የተለያዩ ጫማዎች ሎት 2፡ የቢሮ ፈርኒቸር፤ ኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Sebeta Special Need Education Teacher's College (የሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2018 ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተጠቀሱ ለተለያዩ ሰራዎች እና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1: የፅህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፤ የስፖርት አልባሳትና የተለያዩ ጫማዎች ሎት 2፡ የቢሮ ፈርኒቸር፤ ኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከኮሌጁ ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 128 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የዘመኑን ግብር የገበሩ የቫት ተመዝጋቢና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተዘጋጀው ሰነድ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንከ በተመሰከረለት CPO ከጀርባው የባንኩ ማህተምና ስልክ ቁጥር ያለው በሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ የሚያቀርቡበትን ዋጋ ግልጽ በሆነ የእጅ ፅሁፍ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በተጫራቹ ድርጅት ማህተምና የድርጅቱ ኃላፊ /ተጫራቹ/ ፈርማ ተረጋግጦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 128 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 12B ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4:30 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ያሸነፉት ዕቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ የሎት አንድ (1) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
  10. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0113380660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

* ኮሌጁ የሰበታ መርሐ እውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ይገኛል

 

በኦሮሚያ ት/ት ቢሮ የሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ

 

Save Tender