በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/ 14863 /2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የጨረታ ቁጥር 001/2017ዓ.ም
1. የቢሮ እቃዎች ሎት 1. 7,500.00
2. የጽዳት እቃዎች ሎት 2. 7,500.00
3. የደንብ ልብስ ሎት 3. 10,000.00
4. ቋሚ እቃዎች ሎት 4. 20,000.00
5. ሕትመት ውጤቶች ሎት 5. 2,500.00
6. የሰው መድሃኒት ሎት 6. 20,000.00
7. የሕክምና መሳሪያዎች ሎት 7. 20,000.00
8. ለቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ ሎት 8. 5,000.00
9. ለህንጻ ቁሳቁስን እድሳት ሎት 9. 10,000.00
10. የመስተንግዶ አገልግሎት ሎት 10. 14,000.00
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከጤና ጣቢያው ረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 49 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ስርየተጻፈውን ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበት የንግድ ስራ መስክ/ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን በፅሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈጻጸም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፈበት ዋጋ 10% CPO ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት 3-5፡30 እና 7፡30-9፡30 ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
- ክፍያ የሚፈጸመው ለሚያቀርቡት እቃ ሙሉ በሙሉ በናሙናው መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥና ከንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ሲሆን ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋናውን እና ኮፒውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡30 ሰዓት በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሞሉትን ዋጋ ከነ ሙሉ ሰነዱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን ልክ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንድ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት እቃ ላይ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- ለቋሚ እቃዎች በሚቀርበው በስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ ተጨማሪ ፎቶ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ነጋዴው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከፊትና ከኋላ ማህተም የድርጅቱን ስምና ፊርማ ሳያደርግ ዋጋ ሳይሞላ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ሰነዱ ለውድድር አይቀርብም ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ወይም ድርጅት ማሸነፉ እንደተረጋገጠ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ በተጫራች የሚሞሉ ክፍሎችን እና ዋጋ የሚሞላው ክፍል 4 እና ከፍል 6 የመሙላት ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO የሚያዘው እያንዳንዱን እቃዎቹን ልንገዛበት ከተወሰነው በጀት 0.5% ነው።
- ተጫራቾች የሚሠሩ ጥገና ስራዎችን ቦታው ድረስ መጥታችሁ ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
አድራሻ:- አጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለበለጠ መረጃ፡- 011-2-73-86-34/011-273-87-17
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ
