Tender Detail

Tender Details


የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፤ አላቂ እቃዎች፤ ቋሚ ቢሮ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፤ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች ካርድ እህትመቶች፤ የደንብ ልብስ፤ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፤ አላቂ እቃዎች፤ ቋሚ ቢሮ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፤ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች ካርድ እህትመቶች፤ የደንብ ልብስ፤ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

    1. የ2018 ዓ.ም. ግብር የገበረና የንግድ ፈቃዱን ያደሰ፡፡
    2. ቲን፤ ቲኦቲ፤ ወይም የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
    3. የጨረታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፕኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
    4. ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆነ፡፡
    5. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ) ብር ለወረዳ ገቢዎች በመክፈል ከግዥ ክፍል መግዛት የሚችል፡፡
    6. Withholding Tax (3%) ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ፡፡
    7. በማይክሮ የተደራጁ ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ 2% ሲፒኦ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
    8. በደንብ ልብስ አቅርቦት ላይ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የጨርቁን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    9. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለይቶ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
    10. ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡
    11. የመመዝገቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል፡፡
    12. የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ 2 የስራ ቀን በኋላ ለተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ15ኛ ቀን በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ሊከፈት ይችላል፡፡
    13. የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን እቃ በራሱ ወጭ እስከ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
    14. የእቃው ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
    15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር : 047-342-03-03

 

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender