አርበኞች ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ የመጀ/ደ/ት/ቤት ዓ.ም 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልገሎት ኮምፒውር፣ ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ ማሽን ላፕቶፕ ሥራዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች አላቂ የትምህርት እቃዎች አላቂ የፅዳት እቃዎች የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት/ዝቅተኛ፣ ቋሚ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ የሕንፃ ቁሳቁስ የሕክምና እቃዎች፣ ሕትመት ሥራዎች ቋሚ እቃ ፕላንና ማሽነሪ፣ ሜንቴናንስ ወርክ እንዲሁም ለመስተንግዶ የሚሆን ቆሎ እና ውሃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
አርበኞች ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ የመጀ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
አርበኞች ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ የመጀ/ደ/ት/ቤት ዓ.ም 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልገሎት ኮምፒውር፣ ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ ማሽን ላፕቶፕ ሥራዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች አላቂ የትምህርት እቃዎች አላቂ የፅዳት እቃዎች የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት/ዝቅተኛ፣ ቋሚ እቃዎች፣ ቋሚ እቃ የሕንፃ ቁሳቁስ የሕክምና እቃዎች፣ ሕትመት ሥራዎች ቋሚ እቃ ፕላንና ማሽነሪ፣ ሜንቴናንስ ወርክ እንዲሁም ለመስተንግዶ የሚሆን ቆሎ እና ውሃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም
- በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ፈቃድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የግዥውን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መጨመር ወይም መቀነስ 20% የሚቻል መሆኑን
- ማንኛውም ተጫራች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱ በሚመለከተው ሰው ተሞልቶ ተፈርሞና ማህተብ ተደርጎ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ ጨረታው የሚያበቃው በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ በ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፤
- ናሙና ማቅረብ የሚቻልባቸው ዕቃዎች ላይ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤ ናሙና ማቅረብ ሲገባ ያልቀረበ ከሆነ ግን ተቀባይነት የለውም እንዲሁም ናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩ ዕቃዎች በፎቶ የተደገፈ እና በደንብ በሚታይ መልኩ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት እቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፤
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሀ. ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች / 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/
ለ. ሎት 2 አላቂ የትምህርት እቃዎች /3000.00 /ሦስት ሺ ብር/
ሐ. ሎት 3. አላቂ የፅዳት እቃዎች /3000.00/ ሦስት ሺህ ብር/
መ. ሎት 4 የደንብ ልብስ /3000.00/ ሦስት ሺህ ብር/
ሠ. ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት /1000.00 / አንድ ሺህ ብር/
ረ. ሎት 6 ዝቅተኛ ቋሚ እቃዎች 1000.00 / አንድ ሺህ ብር /
ሰ. ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ማባዣ ማሽን፣ ላብቶፕ (2000.00) ሁለት ሺህ ብር/
ሸ. ሎት 8 ቋሚ እቃ ፕላንና ማሽነሪ 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/
ቀ. ሎት 9 ቋሚ እቃ የሕንፃ ቁሳቁስ /3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/
በ. ሎት 10 የሕክምና እቃዎች /1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
ተ. ሎት 11 ሕትመት ሥራዎች 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
ቸ. ሎት 12 ቆሎ እና ውሃ /2000.00/ ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 13. ሜንቴናንስ ወርክ /3000.00/ ሦስት ሺህ ብር/
በሎት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመስስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ-
እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ VAT በመጨመር ሰነዱ ይቅረብ፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ ከት/ቤቱ ግዥ ቢሮ በስልክ ቁጥር 011 127 51 90 / 011 154 72 04 / ደውለው መጠየቅ ይችላሉ አድራሻ፡- ከራስ ደስታ ከፍ ብሎ ኢየሩሳሌም ሆቴል ፊት ለፊት
አርበኞች ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ የመጀ/ደ/ት/ቤት
