በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት/001/2018 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ.ብር
ሎት 1. የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ 19,000 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 18,000 (አስራ ስምንት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 3. ህትመት 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 4. አላቂ የትምህርት ዕቃዎች /ኬሚካሎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብ ር) ብቻ
ሎት 5. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 6. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ እድሳትና ጥገና 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 8. ኤሌክትሪክ፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች፣ የበር፣ የቧንቧ ውሀ መስመር ዝርጋታ እድሳትና ጥገና 5000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 9. የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 10 ተገጣጣሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) ብቻ
ሎት 11 ውሀ፣ ቆሎ፣ ኩኪስ 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በራሳቸው ምርት ብቻ ካደራጃቸው ጽ/ቤት የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ደብዳቤ በማፃፍ መወዳደር ይችላሉ፡፡ የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት ዕቃ የጨረታ ሰነድ መግዣና የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፣ የውሃ ቧንቧ ጥገና ፣ የበር ጥገና ፣ የጄኔሬተር ጥገና አሸናፊው ለአንድ ዓመት ውል ይዞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በትክክል በማንበብና በመሙላት ማህተምና ፊርማ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በማድረግ ዋጋ መሙያ ሎቱን ብቻ ቀዶ በማውጣት መሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል ስለዚህ የጨረታ ሰነዱ ሁሉም በስርዓት በመሞላት ገቢ መሆን አለበት፡፡
- ዋጋው ከነቫቱ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
