Tender Detail

Tender Details


በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 015 ቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚገዙ ዕቃዎችንብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መሰያ ቁጥር 001/2018

በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 015 ቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚገዙ ዕቃዎችን በግዥ (በሎት)

1. ሎት 1 የደንብ ልብስ--30000 ብር

2. ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 24000ብር

3.ሎት 3 የጽዳት ዕቃ— 23000ብር

4. ሎት 4 ቋሚ ዕቃ— 19000 ብር

በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ በየሎቱ ዓይነት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ሰነዱን ከቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ታሸጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሬ ገላን የመ/ደ/ጀ/ት/ቤት የፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

4. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የመጨረቻ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 1፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሎት 4 ማለትም ለቋሚ ዕቃ በት/ቤቱ የፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች የተወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. የዘገየ በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 015 ቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጀሞ 3 የሚወስደው ከአርቲስት ሀጫሉ ጎዳና (መንገድ) በስተ ምዕራብ በኩል በሚያስገባው ኮሮኮንች መንገድ በኦሮሚያ የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም የሚገኘው ቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- +2511844119

በን/ስ/ላ/ከ/ከ/ወረዳ 015 ቦሬ ገላን የመ/ደ/ት/ቤት

Save Tender