Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 001/2017 ዓ.ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

 

የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር        በኢትዮጵያ ብር            ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር        በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1 ደንብ ልብስ                     10,000 ሎት            ሎት 6 የቢሮ ቋሚ እቃዎች             9,800

ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች         6,400                        ሎት 7 የስፖርት እቃዎች                 3,000

ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች          6,500                        ሎት 8 የላብራቶሪ እቃዎች              1,500

ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ                  9,400                       ሎት 9 የግንባታ እቃዎች            1,700

ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች             4,287.5          ሎት 10 ህትመት                   1,200

ሁሉንም ሎቶች ለሚገዙ 53,787.50 (ሃምሳ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር 50/100)

  1. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶኮፒ ለየብቻው በማሸግ በየሎቱ የተዘጋጀውን የዋጋውን CPO በማካተት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በአስረኛው (10ኛው) ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ማቅረብ ለማይችሉት ቋሚ እቃ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

 

አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በስተጀርባ እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116394253

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ/የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender