Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ወይም ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ተዘረዘሩት አወዳድሮ መግዛትና ማሰፋት ይፈልጋል፡፡

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ወይም ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር በጉ/ክ/ከ/ወ/10/ፋ/ጽ/ቤት/01/2018

 

በጉ/ክ/ከ/ወ/10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ተዘረዘሩት አወዳድሮ መግዛትና ማሰፋት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያዎች 1 ሎት -2 የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት-4 ቋሚ እቃ ሎት-5 የህትመት ስራ ሎት-6 የትራንስፖርቴሽን አገልግሎት ሎት-7 የህንጻ መሳሪያ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰፋት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የሚወዳደሩበትን የንግድ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ የተደረገ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከተፈቀደላቸው የንግድ ዘርፍ ውጪ መወዳደር አይችሉም።
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  5. በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ለሚያቀርቡት ዕቃ ያንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ወይም ያቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ይወሰዳል፡፡
  7. የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በሁለት ፖስታዎች (አርጂናል እና ኮፒ) በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረገ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በጉ/ክ/ከ/ወ/10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 በመ ምጣት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ ሎት 2 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ እና ሎት 3 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ ሎት 4 ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት 5 ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት 6 ብር 10,000.00 / አስር ሺ ብር/ ሎት 7 ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረ (cpo) ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡ (ለሁሉም ሎቶች የሚገዛ ተጫራች በጥቅል ወይም በድምር በአንድ cpo ማቅረብ አይቻልም።
  9. የጨረታ ዝርዝር የሚገልጽ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኮፒ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍሎ መረከብ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን በ10:30 ሰዓት ተዘግቶ በነጋታው 3:00 ሰዓት በፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. አቅራቢዎች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ለእያንዳንዱ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች ናሙና ባላቀረቡባቸው የዕቃ አይነት ላይ መወዳደር አይችሉም።
  13. ተጫራቾች አንድ ዕቃ ላይ አንድ ዋጋና አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው ይህ ባይሆን ተጫራቹ ውድቅ ይሆናል።
  14. ተጫራቾች ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ እንዲያቀርቡ ይገደዳሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ጽ/ቤቱ ለጨረታው ከቀረቡ እቃዎችና አገልግሎቶች ብዛት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ወይም ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20

ሸጎሌ አንበሳ ጋራጅ ዲ/ጎን ለጎን ሸጎሌ ጤና ጣቢያ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011-259-56-93 / 0112-73-77-53 ደውለው ይጠይቁ፡፡

 

በጉ/ክ/ከ/ወ/10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender