Tender Detail

Tender Details


የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/፣ የጽዳት ዕቃዎችና የደንብ ልብሶችን፤ የመኪና ጎማዎች፤ የአገልግሎት ግዥዎች (የኮፒውተርና ተዛማጅ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/፣ የጽዳት ዕቃዎችና የደንብ ልብሶችን፤ የመኪና ጎማዎች፤ የአገልግሎት ግዥዎች (የኮፒውተርና ተዛማጅ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው።
  6. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቶች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከፎቶ ኮፒና ከአሪጅናል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:፡ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ አርዕስት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ቢድ ቦንድ/በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሰርቲፋይድ ቼክ /CPO/ ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ ቀርበው በመውሰድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚሸጡበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒውን በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የዕቃው ጥራት በተገለፀው ስፔስፊኬሽንና በሳምፕሉ መሰረት በመ/ቤቱ ባለሙያዎች የሚመረጥ ይሆናል፣ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራኦች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታውን በኮሚቴ ከመከፈት አያግደውም፡፡ የሚከበሩ የህዝብ በዓላት ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

ጽ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።

ለተጨማሪ መረጃ

ቀበሌ 13 ኢሚግሬሽን ጎን አፈሯ እናት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14

ስልክ ቁጥር 058-222-19-99/058-220-19-70

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን

ባህር ዳር

 

Save Tender