በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለጅ/ጥ/ወ ለሴክተር መስሪያ ቤት ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ እቃዎች እና ለመስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጸ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/201
በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሰንበቴ ከተማ ከአዲስ አበባ በደሴ ከተማ መስመር በ265 ኪ/ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን፡ ለጅ/ጥ/ወ/ በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለጅ/ጥ/ወ ለሴክተር መስሪያ ቤት ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ እቃዎች እና ለመስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች/ አስፔር ፓርት ለአንድ አመት በመዋዋል፤
2. የተለያዩ አይነት የተሸከርካሪዎች ጎማ፤
3. የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጌጣጌጥ/የዲኮር እቃዎች ለአንድ አመት በመዋዋል፤
4. ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ዘይትና ቅባቶች፤
5. እስቴሽነሪ፤ 6. ኤሌክትሮኒክስ፣ 7. የፅዳት እቃ፣ 8. ፈርኒቸር፣ 9. ደንብ ልብስ፤ 10. የእንስሳት መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁስ 11. የህንፃ መሳሪያ 12. የግብርና መገልገያ እቃ 13. የውሃ እቃ፤
በዚሁ መሰረት
- በዘርፉ የተሠማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በዘመኑ የታደሰ መሆን አለበት፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin no/ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- በጨረታ መሣተፍ የሚፈልጉ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከጅ/ጥ/ወ/ገ/ፅ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 ከ 12/12/2017 ዓ.ም እስከ 27/12 /2017 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ፤ በጨረታ ሰነዱ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ያገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ የአቅራቢው ስም እና አድራሻ የሚገልፅ ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት እስከ ከ 27/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ጅ/ጥ/ወ/ገ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ በዚሁ እለት 8፡05 ሰዓት ይታሸግና 8፡15 ሰዓት ተጫራቶች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ይከፈታል፣ በማይገኙ ተጫራቶች ምክንያት የጨረታው መክፈቻ ጊዜ አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታው ናሙና በተጠየቁባቸው ዕቃዎች በናሙናው መሰረት ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤
- ሁሉንም የጨረታ አይነቶች በተናጠል ዋጋ የምናወዳድር ሲሆን፣
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃን በራሱ ሸፍኖ ለግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፣ ለተሽከርካሪዎች መለዋወጫ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለተሸከርካሪዎች ጎማ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለዲኮር እቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለዘይትና ቅባቶች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ለእስቴሽነሪ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የፅዳት እቃ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፈርኒቸር 10,000 /አስር ሺህ ብር ደንብ ልብስ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የእንስሳት መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁስ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ የህንፃ መሳሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የግብርና መግልገያ እቃ 5.000 /አምስት ሺህ ብር/ የውሃ እቃ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 በመክፈልና ደረሰኝ በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው፤
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0331180062/37 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጸ/ቤት
