Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማዎችን፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎችን የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዕቃዎች አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉትን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ለአንደኛ (1ኛ) ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማዎችን፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዕቃዎች አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉትን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-

  1. በንግድ ዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና የንግድ ሥራ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው።
  3. ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በሚሞሉበት ወቅት የዕቃውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (Brand Name and Specification) በግልጽ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚቀርብ ጨረታ ከበቂ መግለጫዎቹ (Specification) ጋር መሆን አለበት፡፡
  5. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስና የጫማዎች ናሙና (Sample) ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የዕቃዎቹን ማጓጓዣ ወጪ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ5ኛው የሥራ ቀን ቀጥሎ እስከ 14ኛው የሥራ ቀን ድረስ ተፈላጊ የመወዳደሪያ ዶክመንቶች ዋናውንና የማይመለስ እንዳንድ ኮፒዎችን በመያዝና 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአባያ ወረዳ የገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ከማንኛውም ተጫራች ከቫት 7.5% (ፐርሰንት) ለመንግስት የሚቀነስ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ዕቃዎችን በማጓጓዝ ሂደት ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ብልሺት መ/ቤታችን ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  • የጨረታው ማወዳደሪያ ቀን በቅዳሜ እና ዕሁድ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጥሎ ባለው ሥራ ዕለት ላይ ይሆናል፡፡
  • መ/ቤታችን ከዲላ ከተማ ከበስተ ደቡብ በኩል 5 ኪ.ሜ ርቀት አስፓልት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር -

09-11-77-21-36/09-16-62-62-32/09-16-40-88-52 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender