Tender Detail

Tender Details


የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ ፈርኒቸሮች፤ ኤሌክትሮኒክሶች፤ የተለያዬ መጠን ያላቸው የመኪና የሞተርሳይክል ጎማዎች ከነ ካለመዳሪያዎቻቸው ፤ የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች እና የተለያዩ የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ ፈርኒቸሮች፤ ኤሌክትሮኒክሶች፤ የተለያዬ መጠን ያላቸው የመኪና የሞተርሳይክል ጎማዎች ከነ ካለመዳሪያዎቻቸው ፤ የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች እና የተለያዩ የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  2. በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ ሃምሣ ሺህ (50,000.00) ብር በሲፒኦ (CPO) ብቻ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ  10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ (በተሰጠው) ጊዜ ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
  5. ተጫራቹ የዕቃው ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
  6. ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  7. ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች እና መሰሎች ናሙና ማቅረብ በሚያስፈልጋቸው አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ የሚችል።
  8. ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ሆኖ ክፍያ ሲከፈለው መ/ቤታችን ግማሹን (7.5) የሚቆርጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ሦስት መቶ (300) ብር ከኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
  11. የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና ግልጽ ሆኖ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ 16ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤፤
  13. ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ሲፒኦ (CPO) ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስ/ቁጥር ፡- 047 441 1128/047 /047 141 0399

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender