የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2018 በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ የምግብ እህሎች (ጥራ ጥሬዎች)፤ አትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ፤ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ፤ የተለያዩ የፅዳት እና አላቂ ዕቃዎች፤ የሲቪል ሰራተኞች ደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ/ እንዲሁም የተመጣጠነ የእንስሳት መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት በ2018 በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ የምግብ እህሎች (ጥራ ጥሬዎች)፤ አትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ፤ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ፤ የተለያዩ የፅዳት እና አላቂ ዕቃዎች፤ የሲቪል ሰራተኞች ደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ/ እንዲሁም የተመጣጠነ የእንስሳት መኖ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ክንውን ቡድን ክፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የተገለፀው ቀን ካላንደር የሚዘጋው ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርበታል
- የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) ማቅረብ ይኖርበታል
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWWppa.gov.et) የአቅራቢነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል
- ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑን በማወቅ ዋጋ ተሞልቶ ናሙና አለማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ለሚጫረቱት እቃ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464414301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል (ዝዋይ)
