የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማ/ማረፊያ ቤት ማዕከል ለ2018 ዓ/ም የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች የምግብ አገልግሎት የሚውሉ ዕህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ አትክልትና ማጣፈጫዎች፣ ለፅፈትና ለፅዳት የሚውል ዕቃዎች ለስልጠና (ለብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ) እና ጥገና፣ ለኤሌክትሪክ ስልጠናና ጥገና፣ ለውበትና ፀር ሥራ ቅባቶችና ዕቃዎች፣ ለልብስ ስፌት ሥራ ስልጠናና ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮምሽን የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያ/ ማረፊያ ቤት ማዕከል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በዚሁ መሰረት በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
ከላይ የተገለፁትን ልዩልዩ ዕቃዎችን በሚወዳደሩበት በዘርፉ የተሰማሩትን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ መደረጉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች፣የዕቃ (የአገልግሎት) አቅራቢዎች ምዝገባ ስለመታቀፋቸው ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም ከግዥ ኤጀንሲ በተለቀቀ የመረጃ መረብ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እንዲሁም የሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በ2018 ዓ.ም ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስከር ወረቀት እና ሌሎች ህጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ስለሆነም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት የቴክኒከና ዋጋው የሚሞላበት ሰነድ በአንድ ኤንቭሎፕ በማድረግና በማሸግ በግልጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና በመፈረም ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾችም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፣ በአማርኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት በድሬዳዋ ማ/ቤት ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 311 በ3ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፣ ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያገኙታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ለማስገባት ስጡ ለሚሜረቱባቸው የዕቃዎች ናሙና አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የቴክኒካልና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱ በመ/ቤታችን ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 311 3ኛ ፎቅ በተባለው ቀንና ሰዓት ተዘግተው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎት ስልክ ቁጥሮች፡- 025 411 6661 ደደውሉ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮምሽን የድሬዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያ/ ማረፊያ ቤት ማዕከል