የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለአምቦ ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ደንብ ልብስ፤ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፤ የመኪና ጎማ፤ ለቴከኒክ ሙያ እና ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 01/2018
የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለአምቦ ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ደንብ ልብስ፤ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፤ የመኪና ጎማ፤ ለቴከኒክ ሙያ እና ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
-
ከተጠቀሰው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ2017 የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ (supplier list) ሆኖ ከሚመለከተው አካል ማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ ታክስ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፡፡
-
ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነጻ የሆና እና የሀገርቱን እና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፡፡
-
ማንኛውም ተጫራቾች በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ሲፒኦ በጨረታው ዶክሜንት ላይ በተገለጸው የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
-
. የጨረታ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበርያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
-
በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል/የድርጅቱ ባለቤት⁄ ሥም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፤ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለጽ አለበት፡፡
-
ተራጫራች የጨረታውን ኦርጅናል ከኮፒው ጋር በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ29/12/2017 8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመክፈት አያስቀርም፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
-
የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል በአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥም ሾርት ኮድ (short code) 518219 ኦብሬተር አይዲ (Operator ID) 182149 ላይ በቴሌ ብር በማስገባት የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የሚሰጣቸውን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በደብዳቤ ከተሰጠበት ጀምሮ በıo ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመስሪያቤቱ ጋር ህጋዊ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊት በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
-
መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ 0112609448/0112364462
የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
