የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ለተለያዩ የሙያ ስልጠና አገልሎት የሚውሉ ዕቃዎችን እና የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ስማት ማረ/ቤት ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ልማት ማረ/ቤት ማዕከል የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ለተለያዩ የሙያ ስልጠና አገልሎት የሚውሉ ዕቃዎችን እና የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ ማለትም ከዚህ በታች የተመለከቱትን
- ለሲቪል ሠራተኞች የተለያዩ አልባሣትን ፤
- የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች -
- የተለያዩ ህትመቶች
- ለሙያ ስልጠና አገልገሎት የሚውሉ ቁሣቁሶች ማለትም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተለያዩ የዕንጨት ሥራ ዕቃዎች የብረታ ብረት ማሰልጠኛ ዕቃዎች የልብስ ስፌት ዕቃዎች፣ የህንፃ ግንባታ ማሰልጠኛ እቃዎች የአውቶ ሞቲቭ ማሰልጠኛ እቃዎች፣
- የተለያዩ የሙያ ማሰልጠኛ እቃዎች
- የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ
- የተለያዩ የእንስሳት ህክምና እቃዎች እና መድሀኒቶች፣
- የተለያዩ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ የጥገና ዕቃዎች
- የግብርና ግብአት እና ፀረተባይ መድሀኒት
- የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች የከብቶች መኖ እና የማገዶ እንጨት አነስተኛ የእጅ ስራ መርጃ መሳሪያዎች እና መጽሐፎች
- የመሰረተ ልማት እድሳት ጥገና አቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ ዕቃዎቹን በጥራት ስማቅረብ የሚያስችል፣
- የዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር በሙያው ዘርፍ የተመዘገበ
- ከገንዘብ ሚኒስቴር አቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብይት መጠኑ ከ800,000.00 /ስምንት መቶ ሺህ ብር / በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች ከገቢዎች ሚኒስቴር ተጨማሪ እሴት ታከለ ቲንነበር ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ተገቢውን ግብር መከፈሉን ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን ሸዋሮቢት ማዕከል ማረ ቤት ግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቹ የተሰጠውን የጨረታ ቅፅ በአግባቡ መሙላት አለበት
- ተጫራቾቹ ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሠነድ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ እንደሚከተለው መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
- ለሲቪል ሠራተኞች አልባሳት ግዥ ብር 10,000.00
- ለጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ ብር 3,500.00
- ለተለያዩ ህትመቶች 1,700.00
- ለተለያዩ የሙያ ስልጠና ዕቃዎች ግዥ ብር 25,000.00
- የህግ ታራሚዎች ቀለብና የወጥ ማጣፈጫ ብር 40,000.00
- የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፤ የማገዶ እንጨት እና የከብቶች መኖ ግዠ ብር 60,000.00
- ለአነስተኛ የእጅ መርጃ መሣሪያዎች እና መፅሀፎች ግዥ ብር 8,000.00
- ለግብርና ግብዓት እና ፀረተባይ ግዥ ብር 25,000.00
- የተለያዩ የእንስሳት ህክምና እቃዎችና መድሀኒቶች ብር 1500.00
- የተለያዩ የቧንቧ የኤሌክትሪክ እና የህንፃ ጥገና ዕቃዎች ግዢ ብር 10,000.00
- የመሰረተ ልማት እድሳት ጥገና እቃዎች ግዥ ብር 15,000,00
ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በተመሠከረ ሠርቲፋይድ ሲፒኦ፤ ቢድ ቦንድ ለ90 ቀን እና በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤት መጥተው ደረሰኝ በማስቆረጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለጨረታው ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ማስያዝ ያለበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሲሆን መስሪያቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማንኛውም የስራ ቀናት በመምጣት ማየት ይችላሉ
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማረሚያ ቤቱ ግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም የሥራ አፈፃፀም በማስያዝ ውል መፈፀም ይገባቸዋል።
- ማረ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ስልክ ቁጥሮች 033 664 0749፣ 033 664 0752 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፋክስ ቁጥር 0336640753
ማሳሰቢያ፡- የዚህ ጨረታ ማስታወቂያ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን፣ ቅዳሚና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ተዘግቶ ይከፈታል።
የሸዋ ሮቢት ተሃ/ስማት ማረ/ቤት ማዕከል
