Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ሸካ ዞን ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0475562232
  • Website
  • Deadline27 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security5,000
  • opening date2025-08-27 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽ/መሳሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽ/መሳሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1ኛ/ ሎት 01 ጽ/መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች

2ኛ ሎት 02 የጽዳት ዕቃዎች

3ኛ ሎት 03 የተለያዩ ፈርኒቸሮችን ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በዚሁ መሠረት

በመስኩ ቀጥታ ግንኙነትና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤

  1. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል 
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 እና ለሎት 03 ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 /አስር ሺህ እንዲሁም ለሎት: 02 /ሁለት/ 5,000 /አምስት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ ብር የሸካ ዞን ፋይናንሰ መምሪያ አካውት ቁጥር 1000510995477 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይት ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በመለየት የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የመንግስት የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገ/ት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል:: የተጫረቾች አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉለውም።
  7. 16ኛ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  8. የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጪ የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በሚገኘው የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ አለበት።
  9. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
  10. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 556 2232 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት

የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender