የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አከሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች በሚሰሩት ፈረቃ የምግብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀድሞ የምግብ ዝግጅቱን በእራስ አቅም በማከናወን አገልግሎቱን ለሰራተኛ ያቀርብ የነበረ ሲሆን የተሻለ አቅርቦትና አገልግሎት ለሰራተኛው ለመስጠት ይረዳ ዘንድ በዚህ የስራ ልምድ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ከ2,200 በላይ ለሆኑ የድርጅታችን ሠራተኞች በፈረቃ የሚመግቡ በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ኮንትራት በመስጠት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በግዥ መለያ ቁጥር (ብ.ግ.ጨ.ቁ BTSC/NCB/Service/02/2018)
የቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አከሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች በሚሰሩት ፈረቃ የምግብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀድሞ የምግብ ዝግጅቱን በእራስ አቅም በማከናወን አገልግሎቱን ለሰራተኛ ያቀርብ የነበረ ሲሆን የተሻለ አቅርቦትና አገልግሎት ለሰራተኛው ለመስጠት ይረዳ ዘንድ በዚህ የስራ ልምድ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ከ2,200 በላይ ለሆኑ የድርጅታችን ሠራተኞች በፈረቃ የሚመግቡ በአገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ኮንትራት በመስጠት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ የሚሣተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፤
3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም የባንክ ያለገደብ ዋስትና ብር50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸነፉት ደግሞ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው ሲ.ፒ.ኦ በቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ወይም “Buluko Textile Share Company" ስም መሆን ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 1.3 ኪ.ሜ ላይ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡ 30- 10፡30 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
8.ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾችና ታዛቢዎች በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0996-672-951 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
አድራሻ፡
ሸገር ከተማ ፣ ፉሪ ከ/ከተማ የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ ስክሲዮን ማህበር