የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ ፤ ሎት 1/ የጽህፈትና የጽዳት መሣሪያዎችን፤ ሎት 2/ የደንብ ልብስ መሣሪያዎች፤ ሎት 3/ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችና፤ ሎት 4 የግንባታ ዕቃ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ ፤ ሎት 1/ የጽህፈትና የጽዳት መሣሪያዎችን፤ ሎት 2/ የደንብ ልብስ መሣሪያዎች፤ ሎት 3/ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችና፤ ሎት 4 የግንባታ ዕቃ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ፤
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ2017 ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች እንዳስፈለጊነቱ በቀረበው አንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ብዛቱን ማዘዝ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ታሽጎ በነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ በባለሙያ ታይቶ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጠር ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፤
- የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ ግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ነው።
- ጨረታው ነሐሴ 8/12/2017 - ነሐሴ 28/12/2017 ሰዓት ቆይቶ የጨረታው ሣጥን ይዘጋል በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 የሚከፈት ሲሆን፣ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን አያስተጓጎልም።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሎት 1/ 15,000 ብር፤ ሎት2 / 15,000 ብር፤ ሎት 3/ 20,000 ብር፣ ሎት 4/ 10,000 ብር፤ ተመላሽ የሚሆን ብር የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው መሣሪያ ብራንድና ማርኩን ግልጽ አድርጎ በሠነድ አያይዞ ማቅረብ አለበት።
- እንደ አስፈላጊነቱ ከተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑ ጋር የውል ስምምነት እስከ መጋቢት 30/2018 ሊቆይ ይችላል።
- በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች በውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
- በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይወጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች ለደንብ ልብስ ጨረታ የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ናሙና /Sample/ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤ በተጨማሪም የሚቀርበው ናሙና የተጠየቀ ብቻ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 17 09 37 49፤
09 22 42 96 65, 09 17 29 95 70
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
