በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የዕቃው ዓይነት ፡-
- የደንብ ልብሶች
- የጽህፈት (ስቴሽነሪ) መሳሪያዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች (Furniture)
- የተለያዩ የመኪና ጎማዎችና የጎማ ካላማዳሪ
- የተለያዩ ሞተርሳይክልና የተለያዩ የሞተርሳይክል ጎማዎች እንዲሁም ካላማዳሪ
- የግንባታ መሳሪያዎች እና የቴክኒክና ሙያ የስልጠና እቃዎች
- የህትመት ሥራዎችን ለማቅረብ የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
መስፈርቱም፡-
- በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ የወጣ ህጋዊ ንግድ ፊቃድ ያለውና የ2017 ዓ/ም ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራችቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና TIN number ማስረጃ ማቅርብ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ባወጣው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ መሰረት ዋጋቸውን በትክክል ሞልተው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማቸውን በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም አድርገው ሙሉ አድራሻቸውን በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ከ 10,000 ብር በላይ ለሆነ ግዥ 2% የመንግስት ታክስ የሚከፈልበት ሆኖ የሽያጭ ደረሰኝ ለእያንዳንዱ ሰክተር መ/ቤት መፃፍ አለበት።
- የመወዳደሪያ ዋጋውን ቫት (VAT) ጨምሮ ያልሰራ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ አስራ አምስት (15) የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከዴጋ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እያንዳንዱን ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቀን 08/12/2017 እስከ 28/12/2017 በ11፡00 ሰዓት ብቻ ዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥን ኤንቨሎፕ በቀን 28/12/2017 11፡30 ሰዓት ይዘጋል።
- አሸናፍው ተጫራች የእቃውን ናሙና በውል መፈፀሚያ ግዜ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የእቃው ማስረከቢያ ቦታ ዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግደታዎች ናቸው።
- የጨረታ ሰነድ የሚከፈተው በቀን 29/12/2017 በ3፡30 ሰዓት በዴጋ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
- የእቃው ብዛት በ20% ሊጨምርም ሊቀንስ የሚችል ሆኖ አሸናፊ ተጫራቾች የተጠየቁትን እቃ ሳያጓድሉ በአንድ ጊዜ ስያስገቡ ብቻ ክፍያ የሚፈፀም መሆኑን ማወቅ አለባቸዉ።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው። ለበለጠ መረጃ ሰልክ 0913267331 ወይም 0966453135 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቡኖ በዴሌ ዞን የዴጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
