ስኬት ባንክ አ.ማ የጽሕፈት እና የጽዳት ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
Siket Bank (ስኬት ባንክ አ.ማ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ስኬት ባንክ አ.ማ የጽሕፈት እና የጽዳት ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ፡- ተራቾች ማሟላት ያለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የስራ ሰዓት /ከሰኞ እስክ ቅዳሜ/ ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የስራ ቀን በባንኩ ዋ/መቤት ቢሮ ቁጥር 406 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈተው የሳምፕል ውጤታቸው ብቁ የሆነ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኮፒ ሰነድ እና አንድ አርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ለዕቃዎቹ ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚመልሱበት ጊዜ በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ልክ ናሙና /Sample/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ቅጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፤ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያሰርዛል፡፡
- አሸናፈው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ይመለስላቸዋል፡፡ ያልታሸገ ሰነድ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፊርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው መክፈቻው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በሚውልበት ቀን እና ሰዓት መሰረት ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ሰዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ፊርማና ማህተም ማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የዕቃ ዓይነት |
Cpo ወይም ባንክ ጋራንቲ |
|
1 |
የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ |
200,000 |
- የባንኩ የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2:30-11:30 ብቻ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታሠር ፊት ፊት
ስልክ ቁጥር: 011 1 27 55 85
ስኬት ባንክ አ.ማ
አዲስ አበባ
