በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ መስሪያ ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የሠራተኞች ደምብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ ፈርኒቸሮች፣ የጽዳት መሳሪያዎች፣ ሕትመትና የሕትመት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማና ከነመዳሪ፤ ሞተር ሳይክል ፣ የሞተር ሳይክል ጎማና ከነመዳሪ፣ የደን ዘሮችና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑ የ2018 ግብር የከፈሉና ፈቃዱን ያሳደሱ
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- 75 ቫት እንሰበስባለን
- አሸናፊዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ TOT (2%) የመክፈል ግዴታ አለባቸው
- በአቅራቢዎች መዝገብ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው
- ለጨረታው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በባቦ ገምቤል ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ከፍለው ሰነዱን ከባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ 10,000 (አስር ሺ ብር) CPO ማስያዝ አለባቸው
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን እስከ ባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የዕቃ ግምጃ ቤት በጊዜው ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታው የፋይናንስና የቴክኒክ ሰነድ ያለምንም ስርዝና ድልዝ ከሞሉ በኋላ በተለያየ ፖስታ አሽገው በኮፒና በአሪጅናል ማቅረብ አለባቸው
- አሸናፊው ዕቃውን በጥራት ማቅረብ አለበት
- ካስፈለገ ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት
- የማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ የሚረዳቸውን አስፈላጊ ዶክመንቶች ሁሉ ማስገባት አለባቸው
- የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 የሥራ ቀናት ከባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማግኘት የምትችሉና በዚያው ቀን የጨረታው ማስገቢያ ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎችና ሕጋዊ ውክልና ባላቸው ፊት በይፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-0571170005 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት