በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 የበጀት ዘመን ለድርጅቱ ሥራ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን የተለያዩ ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ ሃገር አቀፍ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 የበጀት ዘመን ለድርጅቱ ሥራ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፡-
-
- በሎት አንድ /Lot-1/ የቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ዕቃዎችን፤
- በሎት ሁለት /Lot-2/ የተለያዩ የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፤
- በሎት ሶስት /Lot-3/ የተለያዩ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፤
- በሎት አራት /Lot-4/ የተለያዩ የሕንጻ መሣሪያዎችን፤
- በሎት አምስት /Lot-5/ የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር የምችሉ፡-
- በተጠቀሱ ዕቃዎች በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የተሰጠ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- በዘርፉ የተሰጠ መልካም የሥራ አፈፃፀም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ የዓመቱ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀን ድረስ የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው በመግዛት ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ .03 በመውሰድ ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ከተጠየቁ ማስረጃዎች ኮፒ ጋር የእንዱን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ በማስፈር በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም የሕዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይሆናል።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በየለት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ፣ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ማስረጃዎች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦሪጅናል ለየብቻ እንዲሁም የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መገለጽ አለባቸው፤ ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል።
- አሸናፊ ተጫራች የሚለየው ለእያንዳንዱ ዕቃ ያቀረበው የአንዱ ዕቃ ዝቅተኛ ዋጋ መሠረት ያደረገ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 10% ከታወቀ ባንክ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች አሸንፎ ውል የገባባቸውን ዕቃዎች እስከ ድርጅታችን ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው።
- ለአሸናፊ ተጫራች ክፍያ የሚፈፀመው የዕቃዎች የጥራት ደረጃ በባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸ በኋላ እስከ 30 ቀን ድረስ ውል የማይገባ ከሆነ የውል ማስከበሪያ ይወረሳል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-21-83-22-96/09-13-69-83-23 ደውለው ይጠይቁ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
