በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የግንባታና የውሃ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞተር ዘይትና ቅባቶች እና የመኪና ጎማዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ።
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የግዥ ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ እቃዎችን በሎት በማደራጀት ማለትም የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ የስፖርት ልብስና የስፖርት እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የውሀ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የሞተር ዘይትና ቅባቶችና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- ከገቢ ሰብሳቢ ተቋም ግብር የከፈሉበት የግብር ክሊራንስ ማቅረብ ሚችል
- የግዥ መጠኑ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በሚስተ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO)፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Bond) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ለጽህፈት መሳሪያ ብር 30,000/ሰላሳ ሽህ ብር/፣ለጽዳት እቃዎች ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/፣ለቋሚ እቃ ብር 5,000/አምስት ሽህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 6,000/ስድስት ሽህ ብር/፣ለሰራተኛ ደንብ ልብስ ብር 60,000/ስድሳ ሽህ ብር/፣ለስፖርት ልብስና የስፖርት እቃዎች ብር 10,000/አስር ሽህ በር/፣ለግንባታ እቃዎች ብር 40,000/ አርባ ሽህ ብር/፣ለውሀ እቃዎች ብር 40,000/አርባ ሽህ ብር/ ለመኪና መለዋወጫ እቃዎቾች ብር 150,000 /አንድ መቶ አምሳ ሽህ ብር/፣ለሞተር ዘይትና ቅባቶች ብር 20,000/ሀያ ሽህ ብር/ እና ለመኪና ጎማ ብር 60,000 / ስድሳ ሽህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣ የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 ቀናት ኩ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘትይችላሉ፡-
- ከተጫራቾች ሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ዋስትናው ደግሞ የጨረታ ሰነዱ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።በመሆኑም ተጫራቾች በአጠቃላይ የ73 ቀን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ኃሳቡን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኩ/ወ/ገ/ጽ/ ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጧቱ 4:15 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡-
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4:15 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል
- የመጫረቻ ዋጋው ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይደረጋል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ኩ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334480228/0914052246 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Supply of office supplies, cleaning materials, electronics, staff uniforms, sports clothing and equipment, construction and water materials, vehicle spare parts, motor oil and lubricants, and vehicle tyres, organized in lots. Bidders must have a valid trade licence, tax clearance, and VAT registration certificate.
