በኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 በመደበኛ በጀት የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ የደንብ ልብስ እና የስራ ጫማ፣ ፓምፖች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ኦርጅናል የቧንቧ እና HDPE ፊቲንጎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
የኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 በመደበኛ በጀት የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ የደንብ ልብስ እና የስራ ጫማ፣ ፓምፖች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ኦርጅናል የቧንቧ እና HDPE ፊቲንጎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ዋጋ ከvat ጋር ማቅረብ እና በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6:30 ታሽጎ በዕለቱ በ8:00 ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ አስቀድሞ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በኦሮሚያ የገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 ለእያንዳንዱ ሠነድ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ።
- ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ መስሪያ ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጠቅላላ የግዥ ዋጋ 20,000 ከሆነ 3% /withholding tax/ እና ከ20,000 በላይ ከሆነ 7.5% tax ተቀናሽ ይሆናል እንዲሁም አቅራቢው ከቀረበው ከገዛው ጠቅላላ ዕቃ ላይ 0.5% ለውሃ ፈንድ ተቀናሽ ይሆናል።
- እጩ ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ማቅረብ ይኖርበታል::
- ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ከመ/ቤቱ ጋር ውሉን ከፈረመ በኋላ ዕቃውን ከኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በራሱ ማጓጓዣ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ ሥ.ቁ 0221130555
የኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Olengchiti Town Water Supply and Sewerage Service Enterprise seeks to buy electric bajajs, uniforms and work shoes, pumps, electronics, and original pipe and HDPE fittings via open tender. Bidders must hold a valid sector license, updated trade license, tax clearance, TIN, and VAT or taxpayer registration, and be registered on the federal or Oromia supplier list.
