ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮች! ራውተሮች፣ ሰርቨር፣ ፕሪንተሮች እና ዲጂታል ካሜራ እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች እና ፋይል ካቢኔቶች ከታች በተጠቀሱት ሁለት ምድቦች መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
Berhan Insurance S.C (ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ)
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ.
BERHAN INSURANCE S.C
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮች! ራውተሮች፣ ሰርቨር፣ ፕሪንተሮች እና ዲጂታል ካሜራ እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች እና ፋይል ካቢኔቶች ከታች በተጠቀሱት ሁለት ምድቦች መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ምድብ አንድ፡-ኮምፒውተሮች፣ራውተሮች፣ሰርቨር፣ፕሪንተሮች እና ዲጂታል ካሜራዎች ምድብ ሁለት የቢሮ መገልገያዎች ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች እና ፋይል ካቢኔቶች
በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ስነድ ለመግዛት ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ የማይመለስ ተ.እ.ታ ጨምሮ ብር 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ) በኩባንያው ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክበተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል::
4. የጨረታ ሰነዱን በፓስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግንባር ቀርቦ ማስገባት ይኖርበታል::
5. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ለተወዳደረበት በተያያዘው ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል::
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::
7. ጨረታው ነሀሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡3ዐ ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል::
8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት
ወሎ ሰፈር ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7
የሠው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ስልክ 0114674423/46 ወይም 0114704054
