በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ህትመት፣ መስተንግዶ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ፈርኒቸር ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የኪራይ እቃዎች፣ የልብስ ስፌት በመጀመሪያ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ህትመት፣ መስተንግዶ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ፈርኒቸር ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የኪራይ እቃዎች፣ የልብስ ስፌት በመጀመሪያ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
ተወዳዳሪ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ/የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው (tin number)
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ /ብር በባንክ በተመሰረተ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 ብር በመክፈል የካ አባዶ ገደራ ገዛህኝ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውን እና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በወረዳው ፋ/ፅ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡ 00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ የግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡ አሸናፊው ውል ሳይዙ ዕቃ ጭነው ቢመጡ ወደ መጋዝን ማስገባት አይችሉም፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊውና ለተሸናፊ በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንገልፃለን።
- ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስ ቁ. 0118 66-04-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- የካ አባዶ ገደራ ገዛኸኝ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ይገኛል
ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ሎት ለየብቻው ከነሙሉ መረጃው በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
