በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የእቃ ግዥ ጨረታ
ጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 2፡- የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ
- ሎት 3፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ
- ሎት 4፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ
- ሎት 5፡- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 6፡- ለፕላንት፣ ለማሸነሪና ለመሳሪያ፣ እድሳትና ጥገና ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ
- ሎት 7፡- የጥገና ዕቃዎች አቅርቦት ግዥበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤
- ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዥ 500,000.00 ብር
- ሎት 2፡- የደንብ ልብስ ስፌት ግዥ 50,000.00 ብር
- ሎት 3፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ 150,000.00 ብር
- ሎት 4፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ 500,000.00 ብር
- ሎት 5፡- ልዩ ልዩ እቃዎች ግዥ 5000.00 ብር
- ሎት 6፡- ለፕላንት፣ ለማሽነሪ፣ ለመሳሪያ፣ እድሳትና ጥገና ለአንድ አመት ውል የሚፈረም ግዥ 100,00.00 ብር
- ሎት 7- የጥገና ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ 100,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)፣ ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ናሙናዎቻቸውን ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት ዓይነት አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና፤ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፣ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና መግቢያ በር ገብቶ ወደ ግራ እጥፍ ብለው) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የሎት ቁጥሩ፣ አቅራቢው ሰነድ ሊገዛ የተሰጠው ኮድ ፅፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ያልፃፉ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ።
- ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ ሞምላት ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፤ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ወደ አስኮ ሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111112058 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል
