ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለልጃገረድ ሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም 6036 ሮዝ ሞዴስ 4024 250 ግራም እስካይሳሙና እንዲሁም 120 እሽግ (ብዛቱ 28) 5 ቁጥር ABC ዳይፐር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ የሕፃናትና የወጣቶች እንዲሁም የማኀበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለልጃገረድ ሴቶችና ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም 6036 ሮዝ ሞዴስ 4024 250 ግራም እስካይሳሙና እንዲሁም 120 እሽግ (ብዛቱ 28) 5 ቁጥር ABC ዳይፐር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች እና አስፈላጊ ሰነዶችን የሚያሟሉ ከታች በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነድን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
መስፈርቶች/ሰነዶች
- በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቃቸው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ሥራ የምዝገባ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት
- አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንክ የክፍያ ትእዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታውን አሸናፊ ድርጅት የተጠየቁትን ግብዓቶች (ሞዴስ፣ ሳሙናና ዳይፐር) ውል ከተፈራረመበት እለት ጀምሮ በ3 ቀን ውስጥ ማስረከብ የሚችል መሆን ይገባዋል፡፡ እንዲሁም በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ7ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው በተዘጋበት ዕለት 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-157-51-25 ወይም 011-157-08-65 CPO የሚሠራበት Chora for Children and Family Development
አድራሻ:- ሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ድልበር ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት
