በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው መደበኛ በጀትና ለወረዳው የተሰጡ የተለያዩ ፈንድ እና የመሳሰሉት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች 1. አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች 2. አላቂ የጽዳት መገልገያዎች 3. ከአንድ ዓመት በላይ የሚያገለግሉ የቢሮ መገልገያ መሣሪያዎች 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 5. የተለያዩ የቢሮ ፈርንቸሮች 6. የግንባታ ዕቃዎች 7. የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ 8. የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው መደበኛ በጀትና ለወረዳው የተሰጡ የተለያዩ ፈንድ እና የመሳሰሉት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች 1. አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች 2. አላቂ የጽዳት መገልገያዎች 3. ከአንድ ዓመት በላይ የሚያገለግሉ የቢሮ መገልገያ መሣሪያዎች 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 5. የተለያዩ የቢሮ ፈርንቸሮች 6. የግንባታ ዕቃዎች 7. የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ 8. የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ
- ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ተጨማሪ የእሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻል አለባቸው። ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን ከላይ የተገለጹት ዕቃዎች፣ ለተራ ቁጥር 1 ፤ 2 እና 3 ብር 40000 ለተራ ቁጥር 4 ብር 40000 ለተራ ቁጥር 5 ብር 30000 ለተራ ቁጥር 6 ብር 30000 ለተራ ቁጥር 7 ብር 30000 ለተራ ቁጥር 8 ብር 30000 በእጅ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቴክኒካል ዶክሜንት ዋናውን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን በአንድ ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻል ዶክሜንት ዋናውን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ኤንቨሎፕ ላይ የተወዳዳሪውን ማንነት የሚገልጽ ስምና ፊርማ በመጻፍ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሃያ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሐሩ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት በዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው የምዝገባ ጊዜ ከ17/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/12/2017 ዓ.ም የሥራ ቀን ሲሆን በ21/12/2017 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በከፊል ባይገኙም ጨረታውን አያሰናክልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲቀረቡ ዕቃዎቹን በራሳቸው ወጪ እስከ ሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበረያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸውን መስፈርቶች ዕቃዎቹ ወረዳው ባስቀመጠው እስፔስፊኬሽን ለዕቃዎቹ የተሰጠ ዋስትና፣ ለዕቃዎቹ ጥራት፣ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች እስክሪብቶ፣ የኮምፒተር ቀለም፣ ወረቀት፣ ፍሉድ፣ ውሃ፣ አጀንዳ፣ ቦርሣ እና መዝገብ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር - 0917577426 / 0905067099
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
