የበቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዘመን በከተማው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መ/ቤቶችና ት/ቤቶች የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአርሲ በቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር Beko/001/2018
የበቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዘመን በከተማው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መ/ቤቶችና ት/ቤቶች የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ሎት 1 (አንድ) አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 (ሁለት) የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3 (ሦስት) ቋሚ የቢሮ እቃዎች(ፈርኒቸሮች)
- ሎት 4 (አራት) የኤሌክትሮኒክስ ማሳሪያዎች
- ሎት 5 (አምስት) የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ሎት 6 (ስድስት) የኮሌጅ ማስተማሪያ እቃዎች
- ሎት 7 (ሰባት) የስፖርት አልባሳትና ስፖርት እቃዎች
- ሎት 8 (ስምንት) የተለያዩ መኪና ጎማዎች
ስለዚህ ዕጩ ተጫራቾች ሊያውቁት የሚገባቸው መመሪያዎች
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም በስንቄ ሂሳብ ቁጥር 1071508780313 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጽ/ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ከዕቃ ግዢና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው መክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በተናጥል ዋጋ መግለጽ እና በጥንቃቄ ቫትን (VAT) ጨምሮ በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ሲኖርባቸው በተጨማሪም የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ ለኤሌክተሮኒክስ፣ አላቂ እቃዎች (አስቴሽነሪ እቃዎች) እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ ብቻ ለብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) እንዲሁም ለተቀሩት ሎቶች ብቻ ለብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ማቅረብ ይኖርበታል። በማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ድርጅቶች ኦርጅናል የዋስትና ደብዳቤ በህጋዊነት ከደራጃቸው አካል ማቅረብ አለባቸው። የዋስትና ደብዳቤውም ለሚወዳደሩበት ሎት ተጠቅሶ መጻፍ አለበት ።
- ተጫራቾች በሚያቀርባቸው ፖስታዎች ላይ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻቸውን የድርጅታቸውን ማህተምና የሚወዳደሩባቸውን ሎቶች ላይ ቁጥራቸውንና አይነት መጸፍ አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በቆጂ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው ውጤት ከተገለጸለት በኋላ ከ5-15 ቀናት ውስጥ ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላው የግዢ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ለሚያቀርባቸው እቃዎች የአንድ ዓመት ዋስትና በመስጠት ከጽ/ቤቱ ጋር የአቅርቦት ውል ስምምነት መፈራረም ይኖርበታል።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሚሆኑት የቴክኒክ መስፈርትን አልፎ በሚያቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች ለሚያቀርቡት እቃዎች የዕቃ ቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ (Materials Specification) በወረዳው ለእያንዳንዱ ሎት በሚመደብ ቴክኒክ ባለሙያ የዕቃዎቹን ጥራትና ብቃት በማረጋገጥ ገቢ ከሆነ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ
የስራ ቀናት ውጪ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ፡፡
-የጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት ይበረታታሉ።
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0223321178/0223320939 ደውለው መረዳት ይችላሉ
የበቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
