በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 5 የፈርኒቸር ግዥ፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ሎት 7 ህትመት፣ ሎት 8 የኪራይ አገልግሎት፣ ሎት 9 የመስተንግዶ አገልግሎት እና ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 5 የፈርኒቸር ግዥ፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ሎት 7 ህትመት፣ ሎት 8 የኪራይ አገልግሎት፣ ሎት 9 የመስተንግዶ አገልግሎት እና ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ፤
- በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣
- የንግድ ስም ምዝገባ/ምስክር ወረቀት፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ ከገቢዎች የተሰጣቸውን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
በዚሁ መሰረት ለሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች 15,000.00፣ ለሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 15,000.00፣ ለሎት 3 የደንብ ልብስ 1,000.00፤ ለሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 8,000.00፣ ለሎት 5 የፈርኒቸር ግዥ 8,000.00፣ ለሎት 6 የኤሌክትሪክና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች 5,000.00፣ ለሎት 7 ህትመት 5,000.00፣ ለሎት 8 የኪራይ አገልግሎት 5,000.00፣ ለሎት 9 የመስተንግዶ አገልግሎት 5,000.00 እና ለሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና 3,000.00
- የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከቀረበው ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዕቃ ዋጋ 10% CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው።
- ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ በናሙና መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥ እና በንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ መግለፅ ወይም መሙላት አለባቸው።
- የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ /ዘርፍ/ የሚገልጽ ደብዳቤ ካደራጃችሁ ተቋም ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አሸናፊው ለ1 አመት የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116677784 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 ወደ ህዝብ ደህንነት እና አንቆርጫ መውጫ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
