Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክ/ከ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለየዩ አገልግሎቶችን ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም

 

በጉለሌ ክ/ከ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለየዩ አገልግሎቶችን ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1:- የሆቴል መስተንግዶ

ሎት 2፡- ከሆቴል ውጪ መስተንግዶ

ሎት 3፡- ህትመት አገልግሎት

ሎት 4:- መኪኖች ኪራይ

ሎት 5፡- የድንኳን ኪራይ

ሎት 6፡- የሞታርቦና የመድረክ አስቴጅ ኪራይ

ሎት 7፡- የኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና

ሎት 8፡- የመኪና ጥገና

  1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው እቃ ወይም አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ላይ በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድእንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ላይ ወይም አገልግሎቶች ሳምፕል ወይም ናሙና ለመስራቤቱ በማቅረብ የጥራትና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመገማሉ።
  6. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረዝ በመደለዝ ማሻሻያ ማድረግና መለወጥ አይችሉም።
  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያከተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ለሎት 1፡- 20,000 1 ለሎት 2፡- 20,000፤ ለሎት 3፡- 20,000፤ ለሎት 4፡- 20,000፣ ለሎት 5፡- 15,000፤ ለሎት 6፡- 15,000፤ ለሎት 7፡- 15,000 ለሎት 8፡- 20,000 እና የጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
  10.  የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኤንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይበማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  11.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 የጉ/ክ/ከ/አ/ የዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች (ፑል/የአስ/ፋይ/ጽ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  12.  የካፒታል መጠናቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆነ ተጫራቾች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  13.  የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10 ተከታታይ ቀናቶች በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡00 በጉ/ክ/ከ/የዲ/ግ/ስ/ፑል/የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  14.  ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  15.  ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።
  16.  ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  17.  ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
  18.  ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው። የተጫራቾች ማህተም እና የንግድፍቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
  19.  በጨረታ መወዳደሪያ የሚያቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  20.  ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ባይሆን ግን በጨረታ የስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
  21.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡
  22.  ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን መሰረት ናሙና ውይም ሳምፕል ማስገባት ይኖርበታል።

ማሣሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገም በስልክ ቁጥር 0118 121 096

 

ጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

 

Save Tender