Tender Detail

Tender Details


በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳችን ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-01/2018

 

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳችን ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. ለተጠየቁት የሃገር ኢቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በፌዴራል፣ በክልል ወይም ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውና ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትርኒክስ እቃዎች፣ ለጽሕፈት መሃሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸ እቃዎች፣ ለጽዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000073770231 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር፣ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከግበር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ አስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቤቱ ለአመቺነት በመረጠው ቦታ ይከፈታል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቊሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች፣ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ)) ፣ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) ፣ አቅራቢያችን የሚገኝ ባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምቾት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዲክሲስ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ ጽቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖበታል።
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አደራም ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የማሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0223390577/0913349656/0910950695 ደውለው ይጠይቁ።

 

በአርሲ ዞን የዲክሲስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender