Tender Detail

Tender Details


ኢስት ጌት ትራንስፖርት እና ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር አገልግሎት የሰጡ ማለትም፤ ቶዮታ ሲንግል ጋቢና አውቶሞቢል ተሽከርካሪ፣ የቢሮ መገልገያ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣ የብረትና እንጨት ሼልፎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ካዝና፣ የማባዣ ማሽን፣ የብረት ፋይሊንግ ካቢኔቶች፣ የውሃ ማጣሪያ፣ የከባድና አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የሞተር ዘይት መያዣ ጀሪካኖች ቁርጥራጭ አሉሚኒየም ብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው ሎት መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኢስት ጌት ትራንስፖርት እና ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር


 

ያገለገለ ሲንግል ጋቢና ቶዮታ አውቶሞቢል ተሽከርካሪ፣ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማና ሌሎች ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

አክሲዮን ማህበሩ አገልግሎት የሰጡ ማለትም፤ ቶዮታ ሲንግል ጋቢና አውቶሞቢል ተሽከርካሪ፣ የቢሮ መገልገያ ወንበርና ጠረጴዛዎች፣ የብረትና እንጨት ሼልፎች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ካዝና፣ የማባዣ ማሽን፣ የብረት ፋይሊንግ ካቢኔቶች፣ የውሃ ማጣሪያ፣ የከባድና አውቶሞቢል ተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የሞተር ዘይት መያዣ ጀሪካኖች ቁርጥራጭ አሉሚኒየም ብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው ሎት መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች፦

  1. ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ በማቅረብ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ መመሪያና ሰነድ የማይመለስ በሎት ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000533920008 ገቢ በማድረግ ከአክሲዮን ማህበሩ አስተዳደርና ፋይናንስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በማሳየት በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሠዓት ከምሳ ሰዓት በፊት ጠዋት ከ3፡00- 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ 7፡00 -10፡00 ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ 10% (አስር በመቶ) ማስረጃ ያላያያዘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊ ተለይቶ ከታወቀ በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
  6. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ሙሉ ክፍያውን በ 5 ቀናት ውስጥ ከፍሎ ዕቃውን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ ካልሆነ ግን ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ተመላሽ አይደረግም፡፡
  8. አ.ማህበሩ ያዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
  9.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  10. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሸገር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ክፍል ቁጥር 303 ስልክ ቁጥር 0966434458/0911740549

 

ኢስት ጌት ትራንስፖርት እና ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር

 

Save Tender