Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ:-

  1. የፅህፈት መሳሪያዎች
  2. የፅዳት እቃዎች
  3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
  5. ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎች
  6. ሞተር ሳይክሎች
  7. ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ ዕቃዎች
  8. ለቴክኒከና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ ዕቃዎች
  9. የደንብ ልብሶች

በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና፤ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  13.   የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት ያሸነፈበትን ዕቃ ብዛት አባዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት፡፡
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0221161644/2239 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender