Tender Detail

Tender Details

  • Company አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
  • Address ቢሾፍቱ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0114338557
  • Website
  • Deadline24 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security213150.00
  • opening date2025-07-24 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Catering And Cafeteria Services , Kitchen Materials

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 001/2018

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ ቤት የሚውል የተለያዩ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ፣ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ /Suppiler list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 213,150.00 /ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) /የባንክ ዋስትና ደብዳቤ/ ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጎልም።
  8. ተጫራቾች የአሸነፉትን: አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር:- 0114338557/0912065392

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ

 

Save Tender