Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
  • Address ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 57 42
  • Websitehttps://aarevenuesbureau.gov.et/
  • Deadline10 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-11 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር: 0011/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ - የደንብ ልብስ (ለወንድ ሙሉ ልብስ ኮትና ሱሪ፣ ለሴት ኮትና ጉርድ ቀሚስ ወይም ኮትና ሱሪ ተሰፍቶ የተዘጋጀ፣ ሸሚዝ፣ ከረቫት የውስጥ ልብስ እና አጭር የቆዳ ጫማ ለወንድና ለሴት እንዲሁም ደረት ላይ የሚደረግ ተሰኪ ወይም ተንጠልጣይ ሎጎ)

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” በተለያየ ፖስታ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2% በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ፤ C.P.O ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። C.P.O መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተእታ /ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተእታ/ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
  7. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

➢ በስልክ ቁጥር 0115 57 57 42 /0115 57 57 19 በመደወል ወይንም ሜከሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

 

Save Tender