በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለጣ/ወ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግዥ /ንብ/አስ/001/2017
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለጣ/ወ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም የሚፈልግ ሲሆን ግዥው የሚፈጸመው በየሎቱ ዓይነት በጥቅል ሲሆን በከፊሎቹ ዋጋ መስጠት ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት የእንስሳት መድሃኒት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00፤ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ እቃ የኮንትራት ግዥ ብር 20,000.00 ብር፣ ሎት 3. የህትመት አገልግሎት የኮንትራት ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 እና ሎት 4. ለመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል አንፃባራቂ ጃኬት የጨረታ ማስከበሪያ 1,000.00 ብር ማስያዝ አለባችሁ፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/፤ የምታቀርቡት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዝርዝር ጉዳይ የያዘ የእያንዳዱን የጨረታ ሰነድ ከሎት1 እስከ ሎት 4 ያለውን የማይመለስ ብር በሚወዳደሩበት ዘርፍ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በጣ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ያሉት ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦሪጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው በደብረሲና ከተማ ፀደይ ባንክ ህንጻ ጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ሃላፊ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቀባቸዋል፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ4፡29 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ4፡30 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን በ4፡45 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኖቹ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- ነጠላ ዋጋውና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ የነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾች ምርጫ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌቴር ኦፍ ከሬዲት ወይም ለመስሪያ ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ በምትወዳደሩበት ከላይ በየሎቱ ለተጠቀሱት ዘርፍ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ግዥ በጣ/ወ/ደ/ሲና ከተማ በ4ም ፑል ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ በባለሙያ እየተረጋገጠ በስሙ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለይበልጥ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይችላሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 011-6-80-04-32/ 011-6-80-00-68 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
