የአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን የተለያዩ ነገሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ አ.ገ.መ.ኮ.ኤ 01/2018 ዓ.ም
የአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል፡-
የአብከመ የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል፡-
- የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ፤
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ፤
- የሕትመት ስራ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እና 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ እና የህትመት አገልግሎት ግዥ የስራ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ መመሪያው ተካቷል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ አገልግሎቶች ግዥ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በባንክ በመክፈል እና የከፈሉበትን አድቫይስ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት አገልግሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ደ/የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 08/11/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግንባታ ግብዓት አቅርቦት ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በ08/11/2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግንባታ ግብዓት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-2-22-11-07/ 058-3-20-55-51 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፖስታ ቁጥር 382
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
