መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነገሌ ቦረና ቅ/ፅ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢስአ/ግጨ/ነቦ/1/2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው አይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ ለሶስት አመት የሚቆይ |
300.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፦
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነገሌ ቦረና ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በመምጣት 300 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የባለቤትነት ይዞታ ማረገገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራንስ/ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነገሌ ቦረና ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በአዲሱ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ 0941539669/0464451487
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነገሌ ቦረና ቅ/ፅ/ቤት
