የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ ከባድና ቀላል መኪኖች፣ የእርሻ መሳሪያ ማሽኖች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ ጎማ ፣ የተለያዩ ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች እና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ ከባድና ቀላል መኪኖች፣ የእርሻ መሳሪያ ማሽኖች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ ጎማ ፣ የተለያዩ ኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች እና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።
- ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ በክልሉ በሚገኙ ሆሳዕና ፣ ወልቂጤ ፣ ወራቤ እና ዱራሜ ከተሞች ሲሆን ዝርዝር አድራሻ መረጃቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጸዋል።
- በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 /አስራ ስድስት/ ቀናት ለእጩ ተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮው መንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከንብረት ዋጋ ጥናትና ማስወገድ ዳይሬክቶሬት ክፍል በመንግስት የስራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- ንብረቶቹን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ በቆሙበት ቦታ ተገኝቶ ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዳቸውን አሪጅናልና ሁለት ኮፒ ዶክመንቶችን በመለየት በጥንቃቄ ለየብቻ በኤንቨሎፕ) ፖስታ በማሸግ እስከ 16ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው 16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚገዙት ንብረት ዓይነት ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ስም አዘጋጅተው ከመወዳደሪያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 09-13-73-53-67/ 09-10-92-89-86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
