Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-73-62-69
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየተወዳደሩበት ዋጋ 1/4 (ካሽ ወይም CPO)
  • opening date10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና እና የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ሽያጭ ጨረታ (2 ሎት) - በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መኪኖች በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ፡-

  • ሎት አንድ ፡- ገልባጭ የደረቅ ጭነት መኪና
  • ሎት ሁለት ፡- የሰው እና የደረቅ ጭነት መኪና ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ ማንኛውም ተወዳዳሪ መወደደር እንዲችሉ ፤

  1. ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 09/03/2019 ዓ.ም ቀን ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ጅዳ ወረዳ አስተዳደር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት የመኪኖቹን ይዘት በማየት የሚወዳደሩበትን የብር መጠን በመሙላት ማስገባት አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች አንድ ኦርጂናል ፡ አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተጨማሪ እያንዳንዳቸዉ ዶክመንት ላይ ኦርጂናል፤ ኮፒ እንዲሁም CPO በማለት በፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በዚሁ እለት ማለትም በ10/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ይሁን እንጂ ተወዳዳሪዎች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ህጋዊ የጨረታ ኮሚቴዎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የተወዳደሩበትን ጠቅላላ የብር መጠን 1/4 ለጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ከጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. አሸናፊው ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን የብር መጠን ሙሉ በሙሉ በመ/ቤቱ አካውንት ላይ ካስገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ተይዞ የነበረዉ ይመለስለታል።
  9. ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች አሸናፊው ተወዳዳሪ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ አስይዞ የነበረው ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የሚመለስ ይሆናል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከአ/አ ላምበረት መነሀሪያ ጅዳ/ሰርጢ ብለዉ በጣፎ አርባራት መንገድ ተሳፍሮ መምጣት ይችላሉ። ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስ.ቁ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር፡- 011-673 6328

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Sale of two vehicles by court order in two lots: Lot 1 a tipper/dump truck; Lot 2 a passenger and dry-cargo truck. Bidders must inspect the vehicles in person at the Jida district administration compound and submit bids. Documents in original and copy plus a CPO bid bond, separately sealed in one envelope.
Save Tender