የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በአክሱም ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
በአክሱም ከተማ የሚገኘውን የኮርፖሬሽን ህንፃ ለማከራየት በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢ.ግ.ስ.ኮ/ብግጨ/3/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በአክሱም ከተማ የሚገኘውን ህንፃ ለቢሮ አገልግሎት ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት አክሱም ከተማ ቀበሌ 03 ፀሐይ በርኪ እንዳይ እጠን ከአንበሳ ባንክ ጎን ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓም በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር :- 011-4-70-90-95/011-4-42-36-08/
011-4-42-13-12
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር-09-34-09-39-69
አክሱም ቅ/ጽ/ቤት
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
