Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0113659360
  • Website
  • Deadline19 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-19 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት አመት ለሪካፒ ስራ አገልግሎት የሚሰጥ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ የኢኮቴ መሳሪያዎች እና የሰራተኞች የስራ ልብስ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Central Ethiopia Transport & Road Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት አመት ለሪካፒ ስራ አገልግሎት የሚሰጥ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ የኢኮቴ መሳሪያዎች እና የሰራተኞች የስራ ልብስ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት - አንድ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፤ የኢኮቴ ዕቃዎች
  • ሎት - ሁለት የሰራተኞች የስራ ልብስ

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. የተጨማሪ እሴትታከስ/VAT/ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ
  4. የቲን ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት ያለው
  5. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘውትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የዕቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጂናል/ወይም/ ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴከኒከ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦሪጅናል / ሆኖ ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዘውትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በፊት ብቻ ይሆናል፡ ፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ማንኛውም የተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌዴሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውከልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንከ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
  11. ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈለግ ተጫራች ከተዘረዘሩት ዕቃ መጫረት ይቻላል፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ /አቅራቢ/ዎች /ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0113659360 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይምበከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

የቢሮው አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡

 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

 

Save Tender