Tender Detail

Tender Details

  • Company በአ/ቃ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት
  • Address ቃሊቲ መናህሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንጻ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline13 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-13 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በአስተዳደሩ ስር ለሰራተኞች አገልግሎት የሆቴል ወይም ካፍቴሪያ የምግብ የመስተንግዶ አገልግሎቶችን አስተዳደሩ ባስገነባው ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የካፌ አዳራሽ አገልግሎት ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአ/ቃ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 003/2017

 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በአስተዳደሩ ስር ለሰራተኞች አገልግሎት የሆቴል ወይም ካፍቴሪያ የምግብ የመስተንግዶ አገልግሎቶችን አስተዳደሩ ባስገነባው ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የካፌ አዳራሽ አገልግሎት ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣ በዚህም መሰረት

(ሎት 1) ለአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ሰራተኞች የካፍቴሪያ የምግብ አገልግሎት ለመግዛት

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 2% በበባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ጋራንቲ ማቅረብ የሚችሉ። CPO ሲያሰሩ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት ብለው ያስሩ። የጨረታ ማስከበሪያ CPO (ሎት 1)-20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  5. ለካፌ ለሆቴል ለመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ከቫት ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያ ፖስታ በማድረግ አርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ለማስገባት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከገዙት ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. ተጫራቾች ላሸነፉት ግብዓት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 30% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይከፈታል። 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ ቃሊቲ መናህሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንጻ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡-

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

 

በአ/ቃ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender