የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን፣ ማሽነሪዎችን፣ ትራክተሮችን፣ የትራክተር ጋሪዎችን፣ የውሃ ፓምፖችን፣ ጀነሬተሮችን፣ ሚክሰሮችን፣ ቫይብሬተሮችን፣ የተለያዩ ያገለገሉ ኮምፓክተሮችን፤ የቢሮ ዕቃዎችን፤ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎችን፤ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎችን፤ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና ያገለገሉ በርሜሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Construction Corporation (OCC) (የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006/ኦኮኮ-2017
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን፣ ማሽነሪዎችን፣ ትራክተሮችን፣ የትራክተር ጋሪዎችን፣ የውሃ ፓምፖችን፣ ጀነሬተሮችን፣ ሚክሰሮችን፣ ቫይብሬተሮችን፣ የተለያዩ ያገለገሉ ኮምፓክተሮችን፤ የቢሮ ዕቃዎችን፤ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎችን፤ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎችን፤ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና ያገለገሉ በርሜሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ማንነታቻውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ቃሊቲ ከመካኒኮች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ካለው መ/ቤታችን 1ኛ ፎቅ ከኮርፖሬሽኑ ግዢ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ያቀረቡትን ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። ለዕቃዎቹ የቀረቡትን ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡትን ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝቶ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ አዲስ አበባ፤ አለምገና፣ ሱሉልታ፣ ገላን፤ ጉደር፤ ነቀምቴ፤ አዳማ፤ ሀረር፤ ሂር፤ ጭሮ፤ ሻሸመኔ፤ መቱ፣ ጅማ፤ አርጆ፣ ባሌ ሮቤ፣ ዱከም፤ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ንብረት ዋጋ ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋት 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ ዕለት 5፡30 ላይ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- የአሮሚያ ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114-39-00-82 /0973310228/0911127108 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
