Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline05 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-05 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአደጋ መከላከያ እና የሥራ ልብስ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር አስከአአድ ብግጨቁ/006/2017

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የአደጋ መከላከያ እና የሥራ ልብስ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensce)፣
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ኮፒ (VAT Certificate)
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ሕንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን አስገዳጅ የሆኑ ሕጋዊ የሰነድ : ማስረጃዎችን እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0118 21 22 14

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender