በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአቃ/ቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የግዢ መለያ
ቁጥር 03/2017
በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለየሎቱ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች በማየት መወዳደር ይችላሉ።
ሎት 1 6211 / ደንብ ልብስ
ሎት 2 6212 / አላቂ የቢሮ ዕቃ
ሎት 3 6215 / አላቂ የትምህርት ዕቃ
ሎት 4 6218 / አላቂ የፅዳት እቃ
ሎት 5 6313 / ቋሚ የማሽነሪ ዕቃዎች
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር /TIN NO/ ያላቸው
- የዘመኑ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት ፐርሰንት (2 ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁ9 መግዛት ይችላሉ
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በፖስታ በማሸግ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው የሚታሸገው ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን /በስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፤ ጨረታው የሚከፈተው በዛው ቀን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን (በስራ ቀናት) ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት በራሱ ትራንስፖርት ቂሊንጦ 2ተኛ/ደ/ት/ቤት ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በተጨማሪ መምጣት የማይችሉ ከባድ እቃዎችን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና /ሳምፕል/ ላይ ምንም አይነት ማህተም፣ ስልከ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች እንዳይኖር ከወዲው እናሳስባለን፡፡ ምልክት ያለበት ሳምፕል ማስገባት ሳምፕሉን ውድቅ ያስደርጋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% /አስር ፐርሰንት/ ባሸነፉበት ዕቃ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11421605-0922024252/ ብለው ይደውሉ፡፡
አድራሻ ፡- ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት ያለው ት/ቤት
በአቃ/ቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቂሊንጦ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
