በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኛው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 የበጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ቤኬ/አጠ/2ኛ/ደ/ት/02/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኛው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 የበጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት፡- 1- አላቂ የፅዳት መሳሪያዎችና የትምህርት ዕቃዎች፤
ሎት፡- 2- አላቂ የጽዳት እቃዎች፤
ሎት፡-3- የደንብ ልብስ፤
ሎት፡-4- የስፖርት ማቴሪያል፤
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ እና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን መስፈርቱም በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፤ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ከት/ቤቱ ግዥ ክፍል (ፋይናስ ቢሮ) በመምጣት ሰነዱን መግዛት እና መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ዋጋቸውን ከነቫቱ መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ፤ ለሎት ሁለት 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ፣ ለሎት ሶስት 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ እና ለሎት አራት 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ እና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ጨረታ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለያየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ (ሲፒኦ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር አብሮ ይታሸግ።)
- አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ካሸነፉት የጠቅላላ ዋጋውን 10% /አስር ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው የትራስፖርት ወጪ ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ በማምጣት እስቶር ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታው ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ቢጠየቁ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
- የጥቃቅን አነስተኛ የሆኑት ድርጅቶች ባመረቱት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያው በወጣ በ19ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት (አራት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ) ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሆኖ ልዩ ስሙ አራብሳ ሳፋራ አደባባይ ሳይት ሶስት በተለምዶ እንጀራ ቤት አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የሚገኘው የቤኬ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት::
ለተጨማሪ መረጃ በመንግስት የሰራ ሰዓት ብቻ:- በ 09-82-62-32-96 እየደወሉ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
